ምክትል ከንቲባ ወ/ ሮ አዳነች አቤቤ እና የፌዴራል የከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በአፋር ግንባር ተገኝተው ከሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ከሌሎች የጸጥታ ሀይሎችን ጋር የአዲስ አመት በዓልን አሳልፈዋል።
ዛሬ ከሰዓት በአፋር ግንባር ታሪክ ከሰሩት እና ጁንታዉን ጠራርገው ነፃ ባወጡት ቦታ ላይ የአዲስ አመት አቀባበል ድንቅ በሆነ የበዓል ስነ-ስርዓት ማሳለፋቸውን ምክትል ከንቲባ ወ/ ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡
በሰራዊታችን ላይ የሚታየው የሞራል ፣ የቆራጥነት እና የሀገር ወዳድነት መንፈስ ጽናት ቆዩ እንጂ ሂዱ አያሰኝም ነው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ ክብርና ምስጋና ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን እና ለመላው የፀጥታ ሀይላችን በማለት እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
በስነስርዓቱ ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባ እና ሌሎች ከፍተኛ የክልል እና የፌዴራል የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡