ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መገናኛ ብዙሃን አገልግሎት ስርጭት ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፤ ለመላው ቤተሰባቸውና ወዳጆቻቸው መፅናናትን እንመኛለን!!