ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው አውቶብስ ተራ ትልቁ የሃገር አቋራጭ መናኸሪያ ውስጥ ከጠዋቱ 1ሰዓት ላይ ነው።
ተጠርጣሪው የግል ጥቅሙን ብቻ በማስቀደም በህገ-ወጥ መንገድ በማይጠረጠር ሁኔታ ለዚሁ ህገ ወጥ ተግባር ማስፈፀሚያ ባዘጋጀው ከእንጨት በተሰራ ሳጥን ውስጥ በጨርቅ ጠቅልሎ 1ምንሽር ፣ 1 አብራራው ጠመንጃ እና 1 ቱርክ ሰራሽ ኢኮልፒ ሽጉጥ ጭኖ ወደ ጎጃም ሊሄድ ሲል በመናኸሪያው ውስጥ በጫኝና አውራጅ በተደረጁ አጋዥ ኃይሎች እጅ ከፍንጅ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። ግለሰቡ የጦር መሳሪያዎቹን ከደቡብ ኢትዮጵያ ይዞ ማምጣቱነት ለፖሊስ ከሰጠው ቃል መረዳት ተችሏል፡፡
ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር እየተሰሩ ባሉ ስራዎች የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ስለሆነ ይሄው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡