በከተማዋ ቀላል ባቡር መንገዶች እና የቀለበት መንገድ ላይ የሚስተተዋለውን የመንገድ ማቋረጫዎች ችግር ለመፍታት ዘመናዊ የእግረኞች መሻገሪያ ድልድይ ለማስገንባት በሂደት ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ገለጸ፡፡
በድልድዮቹ የግንባታ ዲዛይን እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የኤጀንሲው አመራሮች እና የቻይናው ዥ ያንግ ዚ ዘ ሰከንድ ከተባለ የግንባታ ኩባንያ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በከተማዋ በቀላል ባቡር መንገድ የሚጨናነቅባቸው ጉርድ ሾላ፣ መሪ ሲ ኤም ሲ እና ጎጃም በረንዳ እንዲሁም በአዲስ ሰፈር ሃኪም ማሞ በተባሉ አከባቢዎች የሚገነቡት ዘመናዊ የእግረኛ መሻገሪያ ድልድዮች ግንባታ የሚሆን ጥናት እና ዲዛይን ላይ ነው ውይይት ተደረጓል፡፡
የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ብርሃኑ ግርማ በከተማዋ የምስተዋለውን የትራፊክ ፍሰት በማቀላል እና የመንገድ ደህንነትን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ያደርጋል ብለዋል፡፡
እነዚህ ድልድዮቹ ከዚህ በፊት የተለያዩ አካባቢዎች ተገንብተው ሰው የማይጠቀምባቸው አይነት እንዳይሆን ተገቢው ትኩረት እንደተሰጠው ገልጸው አካል ጉዳተኞችንም ባመከለ መልኩ ምቹ እንደሚሰሩ ኢ/ር ብርሃኑ አመልክተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የቀረበው ጥናት ድልድዮቹ በሚገነቡባቸው ቦታዎች የመሬት አጠቃቀም፣ ወደ መንገዶቹ የሚወስዱ መጋቢ መንገዶች፣ የአውቶቡስ እና የታክሲ መጫኛ እና ማውረጃዎችን፣ የእግረኞች እንቅስቃሴን እና በአካባቢዎቹ የሚስተዋሉ የትራፊክ ፍሰቶችን መሰረት ያደረገ ነው ተብሏል፡፡