የአዲስ አበባ ባህል፣ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በከተማ ደረጃ የቱሪስት ፖሊስ ለማቋቋም የሚያስችል መነሻ ሰነድ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
በዎይይቲ ወቅት የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው እንደተናገሩት የቱሪስት ሰላም እና ደህንነት ለማረጋገጥ እና በቱሪዝም የሚገኘውን ሀብት በማሳደግ ከተማዋ የባህል መዳረሻ እንደመሆኗ በኪነ-ጥበቡ ያላትን እምቅ ሀብት እና በቱሪዝም ዘርፉ ያለውን ብዛት ያለው መስህብ ለቱሪስቱ ተደራሽ ለማደረግ ደህንነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ ሰላም ያለባት ለማደረግ የቱሪስት ፖሊስ እንደሚያስፈልግ በመገንዘብ ወደ ስራ እንደተገባ ገልፀው ቱሪስት ፖሊስ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡
የቢሮው የቱሪዝም መዳረሻ ልማት ቡድን መሪ አቶ ሳምሶን አይናቸው የቱሪስትን ጥበቃ እና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የቱሪስት ፖሊስ ለማቋቋም መነሻ ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት አዲስ አበባ ተፈጥሮአዊና የሰው ሰራሽ የሆኑ ቱሪስት መስህብ ያላት በመሆኑ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ እና ከተማዋ ካላት እምቅ የቱሪስት መስህብ ሀብት ለመጠቀም የቱሪስትን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የቱሪስት ፖሊስ በተቋም ደረጃ ማደራጀት እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።