በዛሬው እለት የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሙልጌታ ጉልማን ጨምሮ የከተማ ደጋፊ አመራሮችና ነዋሪዎች በተገኙበት ለጀግናው መከላኪያ ሠራዊት የስንቅ ዝግጅት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል ።
በመርሃ ግብሩ ላይ ከተገኙት የከተማ ደጋፊ አመራሮች መካከል አቶ ጋትዊች ዎር የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመንግሥት በጀት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንደገለፁት እብሪተኛ የሆነው የጁንታ ሀይል የከተፈተብንን ጥቃት ለመመከት ህዝባችን በብዙ መልኩ ድጋፉን እያደረገ ይገኛል በዛሬው እለትም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በገንዘብ ከሚያደርገው ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልፀው ወረራውን ሙሉ በሙሉ ለመቀልበስና ህልዉናችንን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከድጋፉ ጎን ለጎን የውስጥ አንድነትን ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል ።
የክ/ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ድርጅት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አባይነህ አመርጎ በበኩላቸው በክ/ከተማው ለጀግናው መከላኪያ ሠራዊታችን 60 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ እቅድ ተይዞ 40 ሚሊዮን ብር በጥሬው እንዲሁም 20 ሚሊዮን ብር በግብዓት ድጋፍ ለማድረግ በሁሉም ወረዳዎች እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልፀው ጁንታው ከሚያደርገው የፊት ለፊት ጦርነት በተጨማሪ በሃሰት መረጃዎ ስርጭት የተካነበት በመሆኑ ህዝባችን ትክክለኛውን መረጃ ከመንግስት የመረጃ ምንጮች መውሰድ እንዳለበት ጠቁመዋል ።