በኮሪያዋ ቹንቾን ከተማ ቆይታችን ለጀግኖች ኢትዮጵያውያን የኮሪያ ዘማቾች በቆመላቸው የመታሰቢያ ሃውልት ስር የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ ጀግኖቻችንን ዘክረናል ።
ከራሳቸው አልፈው ለዓለም ሰላም ፣ ለሰው ልጆች ነጻነትና ክብር በጀግንነት በወደቁ አባቶቻችን ታሪክ ኢትዮጵያዊያን በዓለም አደባባይ እንድንኮራ አድርጎናል::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ