የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዙት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው 18 ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ ጋራዥ ግቢ በሚገኝ መጋዘን ውስጥ ሲራገፍ የተመለከቱ የህብረተሰብ ክፍሎች ለፀጥታ አካላት በሰጡት ጥቆማ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ እንደገለፀው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 – 97162 ኢት ተሳቢ ኮድ 3- 29298 ኢት በሆነ ሎቤድ ተሽከርካሪ በህገ ወጥ መንገድ በኮንቴይነር ተጭነው ወደ ሃገር ውስጥ የገቡ በርካታ ልባሽ ጨርቆች ፣ሲጋራ እና የሺሻ መዋስል ወደ መጋዘኑ ውስጥ ሲራገፍ እና የተወሰነው ደግሞ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-31923 ኦሮ በሆነ ዶልፊን ተሽከርካሪ ላይ ሲጫን በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የጋራ ቅንጅት ከነተሽከርካሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ ይገኛል፡፡
የኮንትሮባንድ ንግድ በሃገር ኢኮኖሚ እና በህጋዊ ነጋዴዎች ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ ይህንን ህገ ወጥ ተግባር ለመከላከል እየተከናወነ ባለው ተግባር ህብረተሰቡ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡