በከተማ ደረጃ የተጀመረው “መመረጥ-ተለውጦ ሀገርን ለመለወጥ” በሚል ሰነድ ዙሪያ በተዘጋጀው የአቅም ግንባታ መድረክ እስከ ወረዳ ላሉ አመራር እና ለበታችኛው የፓርቲ መዋቅር አመራርና አባላት ባለፉት ቀናት ሲሰጥ ቆይቷል።
በዚህ የአመራርና አባል አቅም ግንባታ መድረክ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ዙሪያ በዛሬው ዕለት የከተማው ከፍተኛ አመራሮች በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት ማብራሪያ እና የቀጣይ የተግባር አቅጣጫ ስምሪት ሰጥተዋል።
በተከናወነው የአመራር እና አባሉ በግንባታ መድረኩ ወቅት በምርጫ ያገኘነውን ሀገር የመምራት ዕድል በተገቢው መንገድ በመጠቀም ሀገርንና ህዝብን ከማገልገል አንጻር፣ የብልፅግና አመራር እና አባል አሁናዊ ሁኔታ ግምገማ፣ በቅቶ የማብቃት ስትራቴጂ፣ የብልፅግና ፓርቲ ጉዞና የወደፊት አቅጣጫ እንዲሁም ባለፉት የለውጥ ጊዜያት በነበሩ ፈተናዎች እና ድሎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ማከናወን ተችሏል።
ከፍተኛ አመራሩ በማጠቃለያ መድረኩ አመራርና አባሉ ሀገራዊ እና ከተማ አቀፍ አሁናዊ ሁኔታን በሚገባ በመረዳት ቀጣይ ለሚኖሩ ተልዕኮዎች በብቃት እና በጥራት መወጣት በሚያስችል መልኩ ዝግጁ እንዲሆን ለማስቻል የተዘጋጀ የአቅም ግንባታ መድረክ እንደሆነ ገልጸዋል።
በዚህ የግንባታ መድረክ የፓርቲ እሳቤዎችን እና ስነ ምግባር ማዕከል በማድረግ ተግባራዊ ውጤታማነትን ማረጋገጥ የሚያስችል በተለይም አመራሩ አንገብጋቢ የሆኑ የህዝብ ጥያቄዎችን በፍጥነት ከመመለስ እና ከመፍታት አንጻር የህዝብ አገልጋይነት ስሜትን መላበስ የሚያስችል የግንባታ መድረክም እንደሆነ አንስተዋል።
በቀጣይም ፓርቲን ከማጠናከር አንጻር እና የፓርቲን አሰራርና አደረጃጀት ተከትሎ ተግባራትን በብቃት እና በጊዜ በተቋም ደረጃ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ እና አመራሩ እና አባሉ ሀገራዊ አንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከማድረግ አንጻር በግንባር ቀደምትነት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የሚያስችል አቅጣጫ ተቀምጧል።