የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ
የብሔራዊ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚቴ በአደጋ ምላሽ አሰጣጥ እና መልሶ ማቋቋም ተልዕኮ ዙሪያ ለመንግስት አስፈፃሚ አካላት ግልፅ የስራ ስምሪት የሰጠበት መድረክ አካሄዷል።
የብሄራዊ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ደመቀ መኮንን በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት፤ በአሁን ጊዜ መንግስት በወራሪ የጠላት ሃይል ላይ እየወሰደ የሚገኘው የማጥቃት እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በወራሪ ጠላት ላይ ከሚወሰደው የማጥቃት እርምጃ ጎን ለጎን በአገሪቱ የሚደርሱ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለመቋቋም እና ምላሽ ለመስጠት የሚደረገውን ሁለንተናዊ ጥረት በቅንጅት ለመምራት የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁንም አቶ ደመቀ ይፋ አድርገዋል።