በከተማችን በወቅታዊ ሀገራዊና ከተማዊ የዜጎችን በተለይም የወጣቶች እና የልህቃን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ሲካሄድ የነበረው ውይይት በተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች መሪዎች እና መግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች የማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል::
መድረኩ በሀገር ግንባታ በህብረተሰብ ለውጥ ሂደት የዜጎችና የልህቃን ተሳትፎ ወሳኝነት፣ በሀገራችን የተጀመረው ሀገራዊ ለውጦች አወንታዊ ሁኔታ እና እጥረቶች የነበረውን ሚና እና በተጀመረው ለውጥ የሁሉም ዜጋና የልህቃን ገንቢ ሚናቸውን መወጣት የሚያስችል ተሳትፎ ላይ የተደረገውን ውይይት የሚያዳብር መሆኑ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት አመራሩ ህዝቡን በማሳተፍ በአገር ህልውና የተጋረጡ ፈተናዎችን እንደተሻገረው ሁሉ በመነጋገር እና በመስራት በአጭርና በረጅም ጊዜ የሚፈቱ ችግሮችን ለይቶ እየተረባረበ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ለውጡ በርካታ ፍሬዎችንም እያፈራ ያለና ተስፋ የሚጣልበትም እንጂ በተግዳሮቶች ብቻ የተሞላ አለመሆኑን የጠቆሙት ከንቲባዋ የከተማችን የጥንካሬ መሰረት የሀይማኖትና የማንነት ብዝሃነት መሆኑን በመረዳት ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ በበኩላቸው ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና በሚወስደው ትክክለኛ መንገድ ላይ መሆናችንን የተረዱ አካላት ለማደናቀፍ ዛሬም እንደ ትናንቱ ቢረባረቡም ህዝባችንን ይዘን እንሻገረዋለን ብለዋል።
አቶ መለሰ አክለውም ብዝሃነታችንን ለመለያየት በሀይማኖት አክራሪነት፣ በብሄር ፅንፈኝነት እንዲሁም በሂደት እየተመለሱ የሚገኙ ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮችን በማራገብ አገር ለማፍረስ የሚጥሩትን አፍራሽ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በውይይት ማጠቃለያ መድረኩ በሰላም፣ በአንድነት/በህብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነት/ እህትማማችነት የመገንባት፣ የኑሮ ውድነት የማቃለል፣ የስራ አጥነት ችግር የጋራ ጥረት የማድረግ፣ የመንግስታዊ አገልግሎት ችግሮች በጋራ መፍታት ፣ ለልማት ጥያቄዎች መመለስ ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣ የሚዲያን አወንታዊ ሚና የማጠናከር ጉዳዮች ላይ የተናጠልና የጋራ ሚና ለመወጣት የሚያስችል መግባባት ተፈጥሯል: