ባለፉት ሁለት አመታት ለእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ትኩረት በመስጠት አደጋ መከላከል የሚያስችል ዘመናዊ ተቋም ፣ የሰው ሀይልና አሰራር እንዲኖር ተቋሙ ከከተማዋ እድገት ጋር አብሮ በሚሄድ ዘመናዊ ግብዓት እንዲጠናከር ትኩረት ሰጥተን ሰርተናል::
የአደጋ መከላከል ሰራተኞች አደጋ ለመከላከል አደጋ ውስጥ የምትገቡ ፣ የሌላውን ሕይወት ለማትረፍ የራሳችሁን ሕይወት የምትሰጡ ናችሁና ክብር ይገባችኋል።
ህብረተሰባችንም የእሳት አደጋን በመከላከል እና አደጋዎች ሲደርሱ የከፋ ጉዳት ሳያደርሱ በአስቸኳይ ጥቆማዎችን በመስጠት የበኩሉን አስተዋፅዖ እንዲወጣ አሳስባለሁ::
‘የሚጠብቁንን ጀግኖች እናክብር!’
ከንቲባ አዳነች አቤቤ