የዓለም ተሞክሮ እንደሚያሳየው ከተሞች ሲያድጉ በዙሪያቸው ያሉ አርሶአደሮችን እና ገጠራማ ቦታዎችን አካተው አብረው ያድጋሉ እንጂ ህይወታቸውን የሚመሩበት ገቢ እና የመኖሪያ ቦታ ታሳቢ ሳይደረግ ያላግባብ ከይዞታቸው አይፈናቀሉም። በከተማችን አርሶአደሮች በይዞታቸው ላይ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ፣ ደላሎችን ጨምሮ በተለያዩ አካላት ሲጭበረበሩ እና በይዞታቸው የመጠቀም ህጋዊ መብታቸው ሲነፈግ የቆየ ሲሆን ይህን ለማስቀረትና የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ የውይይት መድረኮች አካሂደናል። የአርሶአደሮችን መሰረታዊ ጥያቄዎች በመለየት መሻሻል ያለባቸውን የህግ ማዕቀፎች እና አሰራሮች አሻሽለናል።
በቀጣይም አርሶአደሮች በህግ የተሰጣቸውን ይዞታ የመጠቀምና ያለ አግባብ ከይዞታቸው ያለመፈናቀል መብታቸውን በማስከበር ከከተማዋ እድገት ጋር አብረው በማደግ የልማቱ አካል እንጂ ተፈናቃይ እንዳይሆኑ እንሰራለን።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ