ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በ60 ቀናት ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች በልዩ ሁኔታ ድጋፍ ሲያደርጉበት በቆየው በቂርቆስ ክ/ከተማ በመንግስትና በግል በጎአድራጊ ባለሃብቶችን በማስተባበርና በማቀናጀት ሲያስገነቡት የቆዩት የተለያዩ ፕሮጀክቶች ዛሬ ለምረቃ ይበቃሉ፡፡
ከነዚህም ውስጥ ከ244 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የዘመናዊ ቤት ልማት ፕሮጀክቶች በእርግጥም የከተማችን አዲስ አበባን የቤት ችግር ለመፍታት ትልቅ ተስፋ የተጣለባቸው እንዲሆኑ አስችሏል፡፡
ከእነዚህ ውስጥ በ69 ቀን ተገንብቶ የተጠናቀቀው እና ለ50 አባወራዎች የቤት ችግርን የሚያቃልለው ባለ 11 ወለል ዘመናዊ ተገጣጣሚ ህንፃ በግንባታ ዘርፉ አዲስ ምእራፍ የከፈተ ነው፡፡
በድጋሚ መላው የክ/ከተማው ነዋሪዎች እንኳን ለዚህ ቀን አበቃችሁ!