በአዲስ አበባ ከተማ በ120 ወረዳዎች በ11 ክ/ከተሞችና በከተማ ደረጃ አንድ መድረክ በሁሉም የከተማዋ የአስተዳደር እርከኖች የህዝብ ውይይት መድረኮች ጀምረዋል፡፡
በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚካሄደው ህዝባዊ ዉይይት ህዝቡ በቀጥታ ፊት ለፊት ከፓርቲና ከመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር የሚገናኝበትና ስለአዲስ አበባ ችግሮች የሚመክርበት መድረክ ነው፡፡
በአጠቃላይ በዛሬው ዕለት በከተማችን በሚከናወነው ህዝባዊ ውይይት ከሚወሰደው ግብአት መነሻነት በመጪው ግዜ መንግስት በማህበራዊ፤ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስኮች በቅደም ተከተል መተግበር የሚኖርባችወ የከተማችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚረዱ በርካት ግብአቶች ከህዝብ ይሰበሰባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የከተማውን መድረክ ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባና ብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እንዲሁም አቶ አደም ፋራህ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዘዳንት በጋራ እየመሩት ይገኛል፡፡