ዘንድሮ ፈተና ከወሰዱ 73,385 ተማሪዎች ውስጥ 70.6% ያህሉ 50 ፐርሰንትና ከዛ በላይ በማምጣት ሲያልፉ 61 ሺህ 840 ከሚሆኑ የቀን ተማሪዎች መካከል 50 ሺህ 812 የሚሆኑት ማለትም 82.16% ያህሉ የማለፊያ ውጤቱን በማስመዝገብ ወደ ቀጣዩ የትምህርት እርከን ተዘዋውረዋል።
የዘንድሮው ውጤት ባለፉት አመታት ጋር ሲነጻጸር በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሻሻል የሞዴል ፈተናዎች እና የማጠናከሪያ ትምህርቶችን በመስጠት ፤የተሻለ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት፤ አዲሱን ስርአተ ትምህርት መሰረት ያደረገ ፈተና እንዲዘጋጅ በማድረግ እና መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣታቸው እንዲሁም በትምህርት ቤቶች የተጀመረው የምገባ ስርዓትና ለተማሪዎች እየቀረቡ የሚገኙ ዩኒፎርምን ጨምሮ የተለያዩ የመማሪያ ቁሳቁሶች ለውጤቱ መሻሻል አስተዋጽኦ አበርክተዋል።