የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በዛሬው እለት የሁለተኛው አመት የግድቡ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፈሰስ መጀመሩን የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አስታወቁ።
ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ አሁን በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳስታወቁት ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል ብለዋል፡፡
በቀጣይ ሁለቱ ተርባይኖች ሃይል እንዲያመነጩ ብርቱ ስራዎች እየተሰሩ ነው ፤እናም ይህን በቅርብ ወራት በማጠናቀቅ ልፋታችንን በውጤት እናሳካለን ብለዋል፡፡