የተመረቁት 24 የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና የህጻናት መጫወቻ ስፍራዎችን የፌዴራል እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በቦሌ ፣ በንፋስልክ ላፍቶ ፣ በአራዳ ፣ በአቃቂ ቃሊቲ ፣ በየካ እና በለሚ ኩራ ክፍለከተሞች በመገኘት መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል::
ዛሬ ከተመረቁ የስፖርት ማዘውተሪያ እና የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች ውስጥ ሰባቱ ከመደመር መጽሃፍ ሽያጭ በተገኘ 110 ሚሊዮን ብር ገቢ እና 17ቱ ፕሮጀክቶች ደግሞ በከተማ አስዳደሩ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ ናቸው።