ከ2 ወራት በፊት ከከተማችን ሴቶችና ወጣቶች ጋር ባደረግናቸው ውይይቶች ከመስሪያ ቦታና የስራ ዕድል ፈጣራ ጋር የተያያዘ ኢ-ፍትሀዊነት መኖሩን በነገሩን መሰረት አጣርተን ችግሮች መኖራቸውን በማረጋገጥ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ባልተወጡና የአሰራር ጥሰት በፈፀሙ አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ ተገቢ የእርምት እርምጃ ወስደን በ2389 ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ 12 ሺህ የከተማችን ነዋሪዎች የመስሪያ ቦታ አስረክበናል።
እንዲሁም በሸራ ቤት ሲነግዱ የነበሩት የመስሪያ ቦታ የሚገባቸውን አካል ጉደተኞች እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች መሆናቸውን በማረጋገጥ የመስሪያ ቦታ በመስጠት ስራዎቻቸውን በህጋዊ መንገድ እንዲቀጥሉ አድርገናል።
ዛሬ የመስሪያ ቦታ የሰጠናቸው የአካል ጉዳተኞች፣ ወጣቶችና ሴቶች የመስሪያ ቦታ ማግኘት በራሱ ግብ አይደለምና፣ ተግታችሁ በመስራት ለሌሎች የስራ እድል በመፍጠር ራሳችሁን እንድትለውጡ አደራ ማለት እወዳለሁ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ