አስተዳደሩ የአፍጥር ፕሮግራሙን ከክፍለ ከተማው 10ሩም ወረዳዎች ከተውጣጡ የእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር በጋራ አፍጥረዋል፡፡
በአፍጥር ፕሮግራሙ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ ታላቁን የረመዳን ወር ስናከብር የሚያግባቡንና የጋራ እሴቶቻችን አጠናክረው የሚያስቀጥሉ ባህሎቻችን በማጠናከር ህዝበ ሙስሊሙ በጋራ በአንድነትና በመተሳሰብ ማክበር ይገባል ብለዋል፡፡
የይቅርታ፣የምህረትናየመተሳሰብ የሆነውን የረመዳን ወር ለተቸገሩ ወገኖቻችን በማካፈልና በምህረት ፣በይቅርታና በመተሳሰብ እንዲሁም ለሃገራችን አንድነት በጋራ በመስራት መሆን አለበት ሲሉ ወ/ሮ ቆንጅት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በዛሬው የአፍጥር መርሃ ግብር ከ250 በላይ ለሚሆኑ ሙስሊም ወገኖች በጎ ፈቃደኛ ባለሃብቶችን በማስተባበር መካሄዱን የገለጹት የእለቱን ፕሮግራም ያዘጋጀው የጉለሌ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደግነት ዮሃንስ በቀጣይም በማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ ከ300 በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች ድጋፍ ለማድረግ በመስራት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡፡
አስተዳደሩ የአፍጥር ፕሮግራሙን ከክፍለ ከተማው 10ሩም ወረዳዎች ከተውጣጡ የእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር በጋራ አፍጥረዋል፡፡
በአፍጥር ፕሮግራሙ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ ታላቁን የረመዳን ወር ስናከብር የሚያግባቡንና የጋራ እሴቶቻችን አጠናክረው የሚያስቀጥሉ ባህሎቻችን በማጠናከር ህዝበ ሙስሊሙ በጋራ በአንድነትና በመተሳሰብ ማክበር ይገባል ብለዋል፡፡
የይቅርታ፣የምህረትናየመተሳሰብ የሆነውን የረመዳን ወር ለተቸገሩ ወገኖቻችን በማካፈልና በምህረት ፣በይቅርታና በመተሳሰብ እንዲሁም ለሃገራችን አንድነት በጋራ በመስራት መሆን አለበት ሲሉ ወ/ሮ ቆንጅት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በዛሬው የአፍጥር መርሃ ግብር ከ250 በላይ ለሚሆኑ ሙስሊም ወገኖች በጎ ፈቃደኛ ባለሃብቶችን በማስተባበር መካሄዱን የገለጹት የእለቱን ፕሮግራም ያዘጋጀው የጉለሌ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደግነት ዮሃንስ በቀጣይም በማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ ከ300 በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች ድጋፍ ለማድረግ በመስራት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡