እንደሚታወቀው አጠቃላይ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ሰው ሰራሽ የዋጋ ውድነት በመፍጠርና ምርቶችን በመደበቅ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ህገወጥ ደላሎችንና ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከትናንት በስትያ ግብረ ሃይል አቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት ግብረሃይሉ እያደረገ ባለው ቁጥጥር በዛሬው እለት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ስሙ ሙሉጌታ መናፈሻ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በህብረተሰቡ ጥቆማ በአራት መጋዘን ውስጥ በርካታ መጠን ያለው የምግብ ዘይት ክምችት በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እየሰራቸው ካሉ በርካታ ሌሎች ስራዎች በተጨማሪ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ግብረሃይል በየአካባቢው ሰፊ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል፤
አሁንም ቢሆን ቁጥጥሩ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንና የከተማው አስተዳደር እያስታወቀ የከተማው ነዋሪም እንደተለመደው ጥቆማዎችን በማቅረብ የጋራ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡