ዛሬ የኅብረተሰብ ተሳትፎ ካውንስል የ2015 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ባካሄድነው ጉባዔ የከተማችን ነዋሪዎች በ 4992 ብሎኮች ተደራጅተው ከ39 ሺህ በላይ በሕዝብ የተመረጡ አመራሮች ስራውን አስተባብረው ከመንግስት በጀት ከሰራናቸው 5ሺህ ፕሮጀክቶች በተጨማሪ አንድ ሺህ የሚሆኑ ፕሮጀክቶችን መስራታቸውን አረጋግጠናል።
ከእነዚህም መካከል የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ፣ ድልድዮችን ፣ የውሀ ፍሳሽ ቱቦዎችን ፣ሰፈርን ከሰፈር የሚያገናኙ አነስተኛ ድልድዮችን እንዲሁም በአካባቢ ሰላም ስራዎች ላይ ሕዝቡ በባለቤትነት እንዲሳተፍ ማድረግ ተችሏል፡፡
የስራ ጊዜያችሁን ፣ገንዘባችሁን፣ እውቀታችሁን እንዲሁም ጉልበታችሁን በመስጠት የተሳተፋችሁ ፣የመራችሁ እና ያስተባበራችሁ አካላትን በከተማ አስተዳደራችን ስም አመሰግናለሁ። አሁንም ነዋሪውን በማንቃት በክረምት ወራት ስራ ትኩረት ሰጥታችሁ እንድትሰሩ አደራ እላለሁ!
ሁሉን አቀፍ የኅብረተሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ