በከተማችን የመጀመሪያ የሆነውና ረጅም የመሬት ውስጥ ዋሻ ያካተተ በ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የተሰራው የፑሽኪን ጎተራ መንገድ
በ2015 የመጀመሪያው ሩብ አመት ውስጥ 8.35 ኪ.ሜትር የመንገድ ግንባታ እና 181.4 ኪ.ሜትር የጥገና ስራዎች ለማከናወን ታቅዶ በቅደም ተከተል 20.12 (240.9%) ኪ.ሜትር የግንባታና 195.96 (108%) የጥገና ስራዎች ማከናወን ችሏል፡፡
በተጨማሪም የ2577 የመንገድ መብራት አምፖል ጥገና ስራም፤ 180 ትራንስፎርመር ተከላ፤ 107.8 ኪ.ሜ አዲስ ደንበኞች መስመር ዝርጋታ እና 126.90 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር የመልሶ ግንባታ ስራ መስራት ተችሏል፡፡
ከአዲስ የመንገድ ግንባታ ስራ ጋር በተያያዘ በበጀት አመቱ በ3 ቢሊዮን ብር በጀት 3 ግዙፍ የመንገድ ልማት ስራ ለማከናወን አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ ተከናውኗል
በ2015 በጀት ዓመት በቀን ውሃ የማምረት አቅምን ከ804 ሺህ ሜ.ኩብ ወደ 811 ሺህ ሜ.ኩብ ለማድረስ ግብ ይዘን የመጀመሪያ ሩብ አመት በከተማው ኪስ ቦታዎች ላይ 10 የውሀ ጉድጓዶች ቁፋሮ ተጠናቀዋል ::
10 ሩንም ወደ ስርጭት ለማስገባት እንዲቻል የሚያስፈልጉ የመስመር ዝርጋታና ሌሎች ቀሪ 31 የውሃ ጉድጓድ ቁፍሮ ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛሉ፡፡
የገርቢ ፕሮጀክትን ማስጀመርና ሌሎች አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በመስራት በከተማችን የሚታየውን የውሃ አቅርቦት ሽፍን ለማሳደግ በልዩ ሁኔታ እየተሰራ ነው ::
v በሩብ ዓመቱ የተማሪ ቅበላን ከነበረበት 1,034,373 ወደ 1,050,351 (100.42%) ደርሷል፡፡
v የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራሙና ዩኒፎርም ተጠቃሚነት ሽፋን ከ628,000 ወደ 708,265 በማሳደግ ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ በዕቅዱ እየተሰራ ነው
v አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ በራስ አቅም የመጸሃፍት ዝግጅት ተጠናቆ ተደራሽ የማድረግ ሥራ እየተከነሆነ ነው፡፡
v የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተደራሽነትን ከማሳደግ 24,289 (94.9%) ሰልጣኞችን በመቀበል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
v በ2015 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ለ36,039 የስራ እድል መፍጠር ተችሏል፡፡
ገቢን በተመለከተ
v በሩብ ዓመቱ 16.01 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሏል።
v የታክስ ገቢ 14.78 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ 104.97% ማሳካት ተችሏል፡፡