የጸደቀው በጀት ከአምናው ጋር ሲነጻጸር በ40.21 በመቶ ጭማሪ ያለው ሲሆን ፤በረቂቅ ዓዋጅ ለካፒታል በጀት ትኩረት በመስጠት 77.99 ቢሊዮን ብር ወይም አጠቃላይ ከጸደቀው በጀት 55.59 በመቶውን የሚይዝ ነው፡፡
ለካፒታል በጀት ትኩረት መስጠታችን የከተማዋን ዘላቂ እና መሰረታዊ ዕድገት ለማስቀጠል ፣ሰፋፊ የስራ እድል ለመፍጠር እና ይህን ተክትሎ ለሚመጡ የነዋሪው አዳጊ የልማት እና አገልግሎት ፍላጎቶችን መመለስ እንዲሁም ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥን ታሳቢ ያደረገ ነው።
ይህን በጀት ፍታዊ የገቢ አሰባሰብ እድገት በመተግበር እና ከብክነት የፀዳ አሰራር በማሳከት ነዋሪው የሰጠንን አደራ በትጋት ፣ በታማኝነትና በአገልጋይነት መንፈስ መስራታችንን እንቀጥላለን::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ