ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የተገነባው ሱፍሌ ማልት የብቅል ማምረቻ ፋብሪካ የምረቃ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡
ፋብሪካው በ60 ሚሊየን ዩሮ ወጪ መገንባቱ ታውቋል፡፡
ፋብሪካው በዓመት 60 ሺህ ቶን ብቅል የማምረት አቅም እንዳለው ከኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽንያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በግብርና ላይ የሚሰራ ኢንቪቮ ግሩፕ በተባለ የፈረንሳይ ኩባንያ ስር የሚገኘው ሱፍሌት ማልት በ38 ሀገራት የተለያዩ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች አሉት።