አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ግንቦት 5 ቀን 2014
በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የተገነባው ሱፍሌት ማልት ብቅል አምራች ፋብሪካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሐረመድ በተገኙበት በዛሬው እለት ተመርቋል።
በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በ60 ሚሊየን ዩሮ ወጪ የተገነባው ሱፍሌት ማልት ኢትዮጵያ የተሰኘው የብቅል ማምረቻ ፋብሪካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢብ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የምረቃ መርሐግብር እየተካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፓሬሽን አስታውቋል።