1. ገቢን በተመለከተ
– በግማሽ ዓመት 52.02 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 53 ቢሊዮን(102%) መሰብሰብ ተችሏል፡፡ አፈፃፀሙ ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ18.16 ቢሊዮን ብር ብልጫ ወይም 51.1 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡
2. የጤና ዘርፍን በተመለከተ
– የሆስፒታል አገልግሎት ጥራት ማሳያ የሆነው የፅኑ ህሙማን የሞት መጠን ቀንሷል፤
– የመሰረታዊ የመድኃኒት አቅርቦት ተሸሽሏል
– የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የአባልነት ሽፋንን ለማሳደግ 263,144 አባወራና እማወራዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ 271,038 (103%) መመዝገብ ተችሏል
– የዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የዓይን ህክምና ማእከል በዘመናዊ መልክ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ አሰፈላጊውን ግብአት በማሟላት ስራ እንዲጀምር ተደርጓል
– በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ከፍለው መታከም ለማይችሉ የኩላሊት ታካሚዎች ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ በመፈፀም ነፃ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
– የአገልጋዩንም ሆነ የተገልጋዩን ምቾት እና ደህንነት በሚጨምር መልኩ የወረቀት አልባ የስማርት ጤና ማዕከል እና ደረጃውን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ስራ ተጀምሯል
3. የውሃ አቅርቦትን በተመለከተ
– ከገጸ ምድር እና ከርሰ ምድር 115.29 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ ለማምረት እና ማሰራጨት ታቅዶ 94.35 (82%) ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ በማምረት ማሰራጨት ተችሏል፡፡
– እንዲሁም 4.68 ኪ/ሜትር የከፍተኛ ውሃ መስመር ለመዘርጋት ታቅዶ 4.43 ኪ/ሜትር (95 እጅ)፤ 83.76 ኪ./ሜትር መለስተኛ መስመር ለመዘርጋት ታቅዶ 34.1 (41 እጅ) ተከናውኗል፡፡
4. የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማሻሻል የተከናወኑ ስራዎች
– በመለዋወጫ ችግር ምክንያት ቆመው የነበሩ ከ200 በላይ የሚሆኑ አውቶብሶች በቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ እንዲጠገኑ በማድረግ 46 አውቶቢሶች ወደ ስምሪት እንዲመለሱ ተደርጓል::
– ሌሎች ጥገና ለማድረግ እንኳን በርካታ ችግሮች ያሉባቸው በመሆኑ አዳዲስ 110 የአንበሳ አውቶቡሶች ግዢ ተፈፅሞ ወደ ስምሪት ገብተዋል፡፡
– በየአመቱ ለድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች ወጪ ይደረግ የነበረው 500 እስከ 6ዐዐ ሚሊዮን ብር ኪራይ ለማስቀረት እና በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የሚያሟሉ 200 ዘመናዊ አውቶቡሶች ግዢ የተፈጸመ ሲሆን 100 አውቶቢሶች ስራ የጀመሩ ሲሆን ቀሪዎቹ 1ዐዐ አውቶብሶች በቅርብ ጊዜ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ይሆናል፡፡
– የትራፊክ ፍሰቱን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ እየተሰሩ ካሉ ስራዎች መካከል የትራፊክ ፍሰቱን ከአንድ ማዕከል የመቆጣጠር , የመንገድ ኔትወርክ ስራ እና ዘርፉን ወቅቱ በሚጠይቀው ልክ የማዘመን ስራ እየተከናወነ ይገኛል::
5. የትምህርት ዘርፍ ላይ ከተሰሩ ስራዎች ውስጥ
– የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚነት እና ሽፋን ከነበረበት 600 ሺህ ወደ 700,ሺህ ለማሳደግ ታቅዶ መሉ በሙሉ መፈፀም ተችሏል፡፡
– የምገባ ፕሮግራሙ የተማሪዎችን የመማር ብቃትና ተሳትፎ ከማሳደጉም በላይ ከተማችን በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ሽልማት አግኝተንበታል
– የብዝሃ ቋንቋ ስርዓተ ትምህርት ትግበራ ስርአተ ዝርዝር ማስፈፀሚያን በማፅደቅ በሁለተኛው መንፈቅ ዓመት የተሟላ ዝግጅት ተደርጓል፡፡
– የግብዓትና አቅርቦት ስርጭት በተመለከተ የተማሪ ዩኒፎርም፤ ደብተር እና የመምህራን ጋዎን ማሰራጨት ተችሏል፡፡