የምርት አቅርቦትን በማሳደግ የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ዉድነትን ለማረጋጋት በተሰራው ስራ፤ 170,128 የሰብል ምርት በገበያ ማዕከላት ትስስር መፍጠር ተችሏል፡፡
• የእሁድ ገበያ(Sunday Market) በሁሉም ክ/ከተሞች በ137 የገበያ መዳረሻዎች በማስፋፋት የግብርና ምርቶች ከአርሶ አደሩ ወደ ተጠቃሚው በቀጥታ እንዲደርሱ በማድረግ ሸማቹ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን እንዲያገኝ እየተደረገ ይገኛል
• የመሠረታዊ ፍጆታ ሸቀጦች አቅርቦት ለህብረትሰቡ በፍትሃዊነት ተደራሽ ከማድረግ አንፃር 272,777 ስኳር ማሰራጨት ተችሏል።
• 10.9 ሚሊዮን ሊትር ፓልም ዘይት ማሰራጨት ተችሏል
• 194 ሚሊዮን የሸገር ዳቦ በሸገር ዳቦ በመሽጫ ሱቆች ማሰራጨት ተችሏል
• ከሸገር የዳቦ ፋብሪካ በተጨማሪ የተገነቡት የዳቦ ፋብሪካዎች ቁጥር 25 ማድረስ ተችሏል
• የከተማ አስተዳደሩ በመደበው 1.4 ቢሊዮን የተዘዋዋሪ ብድር በመጠቀም በድምሩ 356,761 ኩንታል ጤፍ በሸማች ኅብረት ሥራ ማህበራት በኩል በማቅረብ ገበያ የማረጋጋት ስራ ተሰርቷል
• ለትምህርት ቤት ምገባ የወቅቱን ኑሮ ውድነት መነሻ በማድረግ በዓመት ተጨማሪ 54ዐ ሚሊዮን ብር ተመድቦ የመጋቢ እናቶችን ጫና የመቀነስ እና የተማሪዎችን ምገባ የተሻለ ለማድረግ የሚያስችል ስራ ተሰርቷል
• በዘላቂነት የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስና ገበያን ለማረጋጋት በአዲስ አበባ የመግቢያ በሮች ማለትም በኮልፌ ፣ በንፋስልክ ላፍቶ ፣ በለሚ ኩራ እና በአቃቂ ክፍለ ከተሞች አራት ትላልቅ ሁለገብ የግብርና ምርቶች ማከፋፈያ ማዕከላት ግንባታ በዚህ በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ 24 ሰዓታት እየተሰራ ይገኛል
. የሌማት ትሩፋት ስራችን አዲስ የልማት ከፍታ ጉዞ በሚል ከጥቅምት 27 ጀምሮ 52,228 ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ስልጠና በመስጠት ወደ ተግባር እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ በተለይ የወተት፣ የዶሮ ስጋ ፣ እንቁላል እና የማር ምርታማነት በማሳደግ እንዲሁም የጓሮ አትክልት በማምረት ያለንን አቅም እና ጸጋ ወደ ተግባር በመቀየር የከተማችንን ነዋሪዎች የኑሮ ጫና ለማቅለል እየተሰራ ይገኛል
. በከተማችን በቀን አንድ ግዜ መመገብ ለማይችሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉ ነዋሪዎች በ15 የምገባ ማዕከላት 30ሺህ ለሚሆኑ ነዋሪዎች የምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ ማድረግ ተችላል::