• የተቋማት ሪፎርም በማካሄድ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን በተመረጡ ተቋማት በመዘርጋት ስማርት ከተማ (SMART CITY) ማድረግ፣ እንዲሁም የአመራሩና የፈፃሚውን ተቋማዊ የመፈጸም አቅም የመገንባት ስራ ተሰርቷል፡፡
• የከተማዋን ገቢ አሰባሰብ በቴሌ ብር እንዲሰበሰብ፤ በE-tax፤ E-filing እና SIGTAS ቴክኖሎጂን በመጠቀም ግብር ከፋዮች ሳይጉላሉ ግብራቸውን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ አሳውቀው እንዲከፍሉ ማስቻል
• የንግድ ፍቃድን በኦንላይን ማደስና አገልግሎቱን የማስፋት ስራ
• በ16 የአገልግሎት ዓይነቶች ከ345 ሺህ በላይ የንግዱ ማህበረሰብ በኦን-ላይን ተጠቃሚ የማድረግ ስራ
• የጤና መረጃ አያያዝ ስርአትን በማዘመን የወረቀት አልባ አገልግሎት በካቲት 12 ሆስፒታል፤ በአበበች ጎበና የእናቶችና ህፃናትና በጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ሙሉ በሙሉ የተተገበረ ሲሆን፣ በራስ ደስታ ሆስፒታል፣ በጋንዲ ሆስፒታል፣ በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታልና በ15 ጤና ጣቢያዎች በከፊል የወረቀት አልባ አገልግሎት ማስጀመር ተችሏል።
• የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ አገልግሎትን የማዘመን ስራ
• የወሳኝ ኩነት አገልግሎት፣ የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር ፋይሎችን ስካን በማድረግ፡ ወደ መረጃ ማስተዳደር ሲስተም ማስገባት ተችሏል፡፡
• በየካ እና በለሚ ኩራ ክ/ከተሞች፡ የመሬትና ወሳኝ ኩነት፣ የግንባታ ፈቃድ አሰጣጥ በዲጂታል ተደርጎ አገልግሎት ተጀምሯል
• በሁሉም ክ/ከተሞች የሰራተኞች የሰዓት ፊርማና የባለጉዳዮች ወረፋ መጠበቂያ ዲጂታላይዝ በመደረጉ የተገልጋዩን እንግልት መቀነስና የአገልግሎት አሰጣጥ ግልፅነትን በመፍጠር የተሻለ ውጤት ማየት ተችሏል፡፡