👉 የጥምቀት በዓል በአደባባይ በህብረት ደምቀን የምንታይበት ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ቅርሶቻችን አንዱና ዋነኛው ነው፡፡
👉 የኢትዮጵያዊ አብሮነት ጥበቦች አምረው የሚገለጡበት በህብረብሄራዊ ቀለማት አምሮ የሚወጣበት ፤እኛነታችን ጎልቶ የሚታይበት በዓል ነው፡፡
👉 የአለም ህዝብ በእውቀቱና በድምቀቱ ተማርኮ ፤ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ከያቅጣጫው የሚጎርፍበት ድንቅና ውብ ትዕይንቶች የሚታዩበት ነው፡፡
👉 የጥምቀት በዓል ጌታ እየሱስ ክርስቶስ አምላክ ሆኖ ሳለ ፤ራሱን ዝቅ አድርጎ በሰው እጅ መጠመቁ ፍፁም ትህትና ያሳየበት ፤ለመዳን ምህረትና ንስሃ አስፈላጊ መሆኑን ያስተማረበት እደሆ ይታመናል፡፡
👉 ከተማ አስተዳደራችን የጥምቀት በዓልን ውበትና ድምቀቱን በመጎናፀፍ ነዋሪዎቿ በጋራ ተሰባስበው የሚያሳልፉበት በርካታ የውጪ ቱሪስቶችን የምታስተናግድበት ፤በሁሉም አቅጣጫ እንደ አበባ ፈክታ ገፅታዋም የሚገነባበት በመሆኑ አስተዳደራችን የበዓሉ ዋና እሴት የሆነውን ትህትና አገልጋይነትን በመላበስ በዓሉ በሰላም ፤በፍቅር በአብሮነት እንዲከበር የእምነቱ አባቶች ከሆኑት ከአገልጋዮቿ ጋር በቅርበት ሲሰራ ቆይቷል፡፡
👉 ወደፊትም በቅንነትና በትትና ማገልገላችንን መቀጠላችንን በዚህ አጋጣሚ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ!!
👉 ደስታችን ዘላቂ እንዲሆን ሰላማችን እንዲፀና፤ ፍቅራችን እንዲጠናከር ፤መከባበራችን እንዲዳብር ፤ህብረታችን እንዲፋፋ ፤ለከተማችን ዘላቂ ሰላምና ለኢትዮጵያችን ፍፁም ሰላማዊ ሁኔታ መስፈን ፤ልማታችንን ለማጠናከር ፤እንደጥምቀቱ እሴት ትህትናና አገልጋይነትን መተሳሰብና መከባበርን ተላብሰን በጋራ መትጋት ይኖብናል፡፡
👉 ብዙ ያልተሰራ የቤት ስራ አለብንና ከቂም ከጥላቻ፤ ከመከፋፈል ርቀን በትናንትና መሰረትነት በዛሬ ተግባራዊነት ነገን እውን ለማድረግ እጅ ለእጅ ተያይዘን ተግተን በመስራት መጪ ጊዜያችን ለሁላችም ብሩህ እናድርገው፡፡
👉 በኛ ለኛ ለኢትዮጵያውያን ቀርቶ ለአፍሪካውያን ብሎም ለአለም ህዝቦ መልካም ቤት ለመሆን በበቃቸው መዲናችን አዲስ አበባም የምታፋቅር እንጂ ፈፅሞ የምታጣላ ከተማ አይደለችም፡፡
👉 በእርግጥ አዲስ አበባን የሚወዳት ሁሉ ለብልፅግናዋ እንዲተጋላት በስሟ የሚነግዱትንም በቃችሁ በጋራ ልንል ይገባልና ፤ሁላችሁንም ለጋራ አላማ በጋራ እንተጋ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ