በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ ፣የአዲስ አበባ ከተማ የባህል ፣ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ፋይዛ መሐመድ ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በማዘጋጃ ቤት በመከበር ላይ ይገኛል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ42ኛ ፤በኢትዮጵያ ደግሞ ለ34ኛ ጊዜ በሚከበረው የዓለም አቀፉ የቱሪዝም ቀን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 5/2014 ዓ.ም ድረስ በከተማዋ የሚገኙ የቱሪስት መዳራሻ ስፍራዎችን የማስጎብኘት ፣በጎዳና ላይ ትርዒቶች ፣ በስፖርት ቱሪዝም እና በመሳሰሉት ልዩ ልዩ ዝግጅቶች የሚከበር ይሆናል።