“ጠዋት መጀመርያ ላይ እንደመጣሁ ፤ቤት ያስረከብኳቸው እናት ቤታቸውን ላይ መጥቼ ገብቼ መውጫ አጥቼ ነበር አልረሳውም፡፡ ገብቼ መውጣት ነው ያቃተኝ፡፡ እሳቸው ግን ይኖሩበነት ነበር፡፡ ይሄ ቀላል ነገር እንዳልሆነ እንድንመለከተው ነው፡፡
ከተማችን ደግሞ የሃብታሞች ብቻ አይደለችም፡፡ከተማችን ድሆችም የሚኖሩባት ናት፡፡ በሁለቱ መሃከል ያለውን ምጥጥን ጠብቀን መሄድ አለብን፡፡ ሃብታሞች በመኖራቸው እንደዚህ አይነት ድጋፍ ይደግፉናል፤ ከጎናችን ይቆማሉ፤ ድሆችን ደግሞ በጋራ ተባብረን ደግፈን የበለጠ ከተማቸውን ወደው ተስፋቸው ለምልሞ በአንፃራዊነት የተሻለ ህይወት እንዲኖሩ ማድረግ እንችላለን፡፡”
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለት አዳዲሶቹን ቤቶች ባስመረቁበት ሰአት የተናገሩት።
ይህ ምስል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ ለተመረቀው ቤት የመሰረት ድንጋይ ለማስቀመጥ በመጡበት እለት ከታች አዲስ ቤት የተረከቡት እናት ቤት ገብተው የቤቱን ሁኔታ አይተው በወጡበት ወቅት የተወሰደ ነው፡፡