የሁላችንም የኢትዮጵያዊያን መዲና የሆነችው አዲስ አበባችንን የቱሪስም መዳረሻ እናድርጋት። የትጋት፣ የስራ አክባሪ፣ የፍቅር እና የአብሮነት ተምሳሌት ከሆኑት የከንባታ ጠንባሮ ህዝቦች ልማት ማህበር 25ኛ አመቱን አከበረ። እንኳን አደረሳችሁ! የከንባታ ጠንባሮ ህዝቦች የልማት ማህበር የ25 ዓመት የብር ዕዮቤልዩ በዓል መዝግያ፣ ግንዛቤ መፍጠርያ እና የንቅናቄ ፕሮግራም ዛሬ ከፍተኛ የፌደራል እና የከተማ አመራሮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተካሂድዋል። አዲስ አበባችን የኢትዮጵያዊያንን ተዝቀው የማያልቁ ቱባ ባህሎቻች፣ ቅርሶች እና ታታሪነት ማሳያ ማዕከል እንድትሆን ባቀድነው መሰረት በትጋቱ እና በታታሪነቱ የሚታወቀው ከንባታ ጠንባሮ ህዝብ ማንነቱን እና እሴቱን የሚያሳይበት የባህል ማዕከል መገንብያ ቦታ በጠየቁበት መሰረት የከተማ አስተዳደሩ በአፋጣኝ ምላሽ በመስጠት በአዲስ አበባችን የባህል ማዕከል መገንብያ የሚሆን መሬት አስረክበናል።