የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር “ነገን ዛሬ እንትከል!” በሚል መሪ ቃል ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ የፌደራል እና የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።