የከተማችንን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ የፀጥታ አካላት ልዩ ልዩ ተግባራትን እያከናወኑ ይገኛል፡፡ በዚህም አበረታች ውጤት ማግኘት ተችሏል፡፡
ዓርብ መስከረም 21 ቀን 2014 ዓ.ም ከጧቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ ከፀጥታ ስራ ጋር በተያያዘ ለሚከናወን ተግባር በመስቀል አደባባይ እና በዙሪያው የሚገኙ መንገዶች ለተወሰነ ሰዓት ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት፦
• ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወሎ ሰፈር አደባባይ
• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚውስደው መንገድ 22 ማዞሪያ
• ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት
• በቸርችር ጎዳና ፒያሳ ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ
• ከጦር ሃይሎች በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
• ከጀሞ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሳር ቤት አደባባይ
• ከሳሪስ ፣ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አጎና ሲኒማ
• ከቦሌ ፣ አትላስ ቅዱስ ዑራኤል ቤ/ከርስቲያን የሚወስደው መንገድ ኤድናሞል አደባባይ
• ከአዋሬ ወደ ካሳንቺስ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ
• ከልደታ በጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ የሚወስደው መንገድ አብነት ፈረሰኛ አካባቢ
ነገ መስከረም 21 ቀን 2014 ዓ/ም ዓርብ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ለጊዜው መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ መሆናቸውን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡