ከናኒ ቤኛ በተጨማሪ ሌሎች 7 ተጠርጣሪዎችም ተይዘዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ለሽብር አላማ ሊያውሉዋቸው የነበሩ የቀድሞ መከላከያ የደንብ ልብስ፤ በርካታ ቁጥር ያለው የተለያዩ የባንክ የሂሳብ ደብተሮች፤ የተለያዩ የባንክ ኤቲኤም፤እና የተለያዩ ሰነዶች በተከራዩበት ቤት ውስጥ ተገኝተዋል፡፡
በከንቲባ ጽ/ ቤት፤ በመከላከያ መረጃና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ በተሰራ ስራ ነው ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የአከራይ እና ተከራይ ውል ሳይኖራቸው በአንድ ክፍል ቤት ውስጥ 8 ሆነው ሲኖሩ እንደነበረ ተገልጿል፡፡
አከራዮች ቤታቸውን ሲያከራዩ የተከራዮች ማንነት የሚገልጽ መረጃ ጠይቀው ማከራየት እንደሚገባቸው የጸጥታ ግብረ ሃይሉ አሳስቧል፡፡
ህብረተሰቡ ጸጉረ ልውጦችን ሲያገኙ በአቅራቢያቸው ያሉ የጸጥታ ሃይሎቸች ማሰወቅ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡