አራተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የማስጀመሪያ መርሃ ግብርን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በይፋ አስጀምረዋል።
7 ነጥብ 6 ቢሊዮን ችግኞች የተዘጋጁበት አራተኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በጉለሌ የእጽዋት ማእከል ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
በመርሀ ግብሩ ላይ ሚኒስትሮች፣ የክልል ፕሬዝዳንቶች፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ ዶክተር ሙላቱ ተሾመ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳፋኪ መሃማትን ጨምሮ የውጭ አገር ዲፕሎማቶች አትሌቶችና ሌሎች ተሳትፈዋል።