የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአራተኛው ዙር የጽዳት ንቅናቄ ማስጀመሪያ ንቅናቄ ዛሬ በሁሉም ክ/ከተሞች ተጀምሯል።
የፅዳት ስራ በአዲስ አበባ ከተማ ባህል እንዲሆን እየሰራ ያለው ከተማ አስተዳደሩ ይህ በአራተኛ ዙር የተጀመረው የፅዳት ንቅናቄ ብሎክን ማእከል ያደረገ ለ3 ወራት የታወጀው የፅዳት ዘመቻ አካል ነው፡፡ ፅዳቱም በየሳምንቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
በፅዳት ዘመቻው በየአካባቢው ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ ነዋሪዎች ታዋቂ ሰዎች ፤ አመራሮችና ፤የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዲሁም መከላከያ አበላት ተሳትፈዋል፡፡