የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አራት ልጆቿን በጫካ ውስጥ ስታሳድግ ለነበረች እናት የመኖሪያ ቤትና ሙሉ የቤት ቁሳቁስ የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ በተገኙበት አበርክቷል፡፡
ወ/ሮ ሰሚራ ይልማ ከዚህ በፊት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን አዲስ ምዕራፍ ፕሮግራም ላይ ልጆቿን በጫካ ውስጥ ከጅብ እየታገለች እያሳደገች እንደሆነ ተናግራ የነበር ሲሆን የክፍለ ከተማው አስተዳደር ከወረዳ አንድ አስተዳደር ጋር በመተባበር በ478ሺ ብር ወጪ ባለ 3 ክፍለ ቤት ከነ ሙሉ የቤት ቁሉ ቁሳቁስ ፤ የአንድ ወር አስቤዛ፤ የ4 ልጆቿ ትምህር ቤት እንዲሁም ለወይዘሮ ሰሚራ ቋሚ የስራ እድል እንድታገኝ ድጋፍ አድርጓል፡፡
አቶ መለሰ ዓለሙ የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ቤቱን ባስከረቡበት ወቅት እንደገለፁት በከተማዋ ብዙ አስቸጋር ህይወት የሚመሩ ወገኖች መኖራቸውን ገልፀው ባቅማችን መድረስ ከቻልን የብዙዎችን ህይወት እንቀይራለን ለዚህ ቤተሰብ ሀገር ደርሷል ሀገር ማለት ቤተሰብ ነው ሲሉ ገልፀው የሁላችንንም ሀገር የሆነችውን ኢትዮጵያን ሰላም ለመጠበቅ እንጠንክር የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል ረዲ በበጎ ተግባሩ የተሳተፉትን አመስግነው መረዳዳትና መተጋገዝ ከቻልን የበርካቶችን ህይወት እንደምንቀይር ይህ ተግባር ማሳያ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በተያያዘ ዜና “በጎነት ለዘላቂ ወንድማማችነት!” በሚል መሪ-ቃል በክፍለ ከተማው የፋሲካና የረመዳን የፆም ወርን ምክንያት በማድረግ ለ104 አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ተከናውኗል።