በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት እያደረጉ ነው።
የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ባዘጋጀው በዚህ ወቅታዊ ሃገራዊ ውይይት ላይ በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችና የፓርቲው አመራሮች እየተሳተፉ ነው።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በአሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል በግፍ ለተጨፈጨፉ ንጹህን ሀዘናቸውን ገልጸዋል።
አሸባሪው ህወሓት የትግራይን ህዝብ ማሰቃየቱ ሳይበቃው በአፋር እና በአማራ ክልል እያደረሰ ያለውን ግፍና መፈናቀል በጽኑ እንደሚያወግዙ በከተማዋ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች መናገራቸወን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።