የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ የጽ/ቤቱ ም/ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ እና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይመር ከበደ በቦሌ፣ በየካ እና በአራዳ ክፍለ ከተሞች በመገኘት አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ጉብኝት አከናውነዋል፤ ከክፍለ ከተማ አመራሮች ጋርም ተወያይተዋል ።
የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት እየተከናወኑ ባሉ የፖለቲካ እና የድርጅት ስራዎች አበረታች ተግባራትን መመልከታቸውን በመግለጽ ስኬታማ የሆኑ ተግባራትን ተሞክሮ ቀምሮ የማስፋት ተግባርም ተጠናክሮ መሰራት እንዳለበት አስረድተዋል።
በተጨማሪም በብልፅግና እሳቤ ላይ የተመሰረተ የዓላማ አንድነትን በመገንባት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠልና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ እንደሚገባም አቶ ሞገስ አስገንዝበዋል።
በአስተሳሰብ ቀረፃ እና በተቋም ግንባታ እየተሰሩ ከሚገኙ አበረታች ጥረቶች በተጨማሪ በክፍለ ከተሞች የተጀማመሩ የከተማ ግብርና፣ የሌማት ትሩፋትና መሰል የልማት ስራዎችን እና የቴክኖሎጂ አቅምን በመጠቀም ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓቶችንም የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ጎብኝተዋል።