አንዳንድ የምዕራባዊያን ሀገራት ፌዴራል-ኮንፌደራል ኃይል በሚል አካሄድ በኢትዮጵያ አሻንጉሊት መንግስት ለመመስረት የሚያከናውኑትን ሴራም አውግዘዋል።
ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መግለጫ ሰጥቷል።
ኢትዮጵያ በረጅም ታሪኳ ፈተናዎችን በድል የተሻገረች፣ ዜጎቿም በሉዓላዊነትና በነፃነት ጉዳይ የማይደራደሩ መሆናቸውን የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱ የጋራ ምክር ቤት አስታውቋል።
የአሸባሪው ህወሃት ወራሪ ኃይል በወረራ በፈጸመባቸው የአፋርና አማራ ክልሎች በርካታ ውድመት ማድረሱን ተመላክቷል።
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ለገጠማት ችግር ምንጩ በስልጣን ጥም የሰከረውና ሰብዓዊነት የሌለው አሸባሪው ህወሃት መሆኑንም ምክር ቤቱ ገልጿል።
የጋራ ምክር ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ አካሉ፤ ለህልውና ዘመቻው ውጤታማነት ከወረዳ እስከ ቀበሌ ባሉት መዋቅሮች የሃብት አሰባሳቢ፣ የደህንነትና ጸጥታ እንዲሁም የአደረጃጀት ኮሚቴ በማቋቋም ምክር ቤቱ ወደስራ መግባቱን ገልጸዋል።
ለዚሁ ተፈፃሚነትም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ወደ ግንባር በመዝመት፣ ለሰራዊቱ ደጀን በመሆንና የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ነዋሪዎቹ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች ሳይረበሹ የከተማዋን ሰላም መጠበቅ እንዳለባቸውም አመላክተዋል።
አንዳንድ የምዕራባዊያን ሀገራት በኢትዮጵያ አሻንጉሊት መንግስት ለመመስረት የፌደራል-ኮንፌደራል ኃይል በሚል በኢትዮጵያዊያን ላይ ሊጭኑ የሚሞክሩትን መፈጭርጨርም አውግዘዋል።
ለዚሁ እኩይ ዓላማ የሚያጎበድዱ ባንዳ ወገኖችም ከክህደት ተግባራቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ አሳስበዋል።
ኢዜአ
_ አካባቢህን ጠብቅ፣
_ ወደ ግንባር ዝመት፣
_ መከላከያን ደግፍ።