አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምስጋና አቀረቡ።
ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር አብሮ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
“ክቡርነትዎ ከእርስዎ ጋር በመሆን የሁለቱን አገራት ዲፕሎማሲያዊና የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎችን እሰራለሁ” ብለዋል ፕሬዝዳንቱ በዚሁ መልዕክታቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለፕሬዝዳንቱ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ማስተላለፋቸውም ይታወሳል።