በከተማችን ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የመሰረት ድንጋይ ከተቀመጠላቸው ሃያ ቀናትን ያስቆጠሩት የቤት ግንባታ ፕሮጀክቶች በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ደረጃ በመፋጠን ላይ ይገኛሉ፡፡
ተለምዷዊውን የግንባታ ሂደት ታሪክ በመቀየር ሌትና ቀን በመስራት ለህዝባችን አዲስ የስራ ባህል ፤አዲስ የመለወጥ ወኔና የአመራር ሰጪነትና ክትትል እንዲሁም በፕሮጀክቶች መጓተት የሚፈጠረውን የተበላሸ አሰራር የዜጎች መጉላላት በማስቀረት በመሃል አዲስ አበባ ዘመናዊና ለነዋሪዎች ምቹ ቤቶችን ሰርቶ ለማስረከብ ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡
ይህ ስራ በሁሉም ክ/ከተሞች በዚሁ የስራ ዲሲፕሊን በትጋትና በጥብቅ ክትትል እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ከተማችን አዲስ አበባ እንደ ስሟ ውብ እና አዲስ ትሆናለች!!