ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከተቋሙ የቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን ጋር በመሆን የሚዲያውን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ስላለበት ሁኔታ በተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በሚዲያው ዘርፍ ተወዳዳሪ ለመሆንና የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማርካት እያካሄደ ላለው የማሻሻያ ስራ ውጤታማነትም አስተዳደሩ አስፈላጊው ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡
በተለይም የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን በማሟላትና አመቺ የስራ ሁኔታ በመፍጠር ረገድ ሚዲያው የሚያስፈልገውን ድጋፍ ከተማ አስተዳደሩ እንደሚያደርግ ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ተደራሽነቱን፤ የስርጭት ጥራቱን እና ይዘቶቹን በማሻሻል በሚዲያው ዘርፍ ተወዳዳሪ ለመሆን ዘርፈ ብዙ የማሻሻያ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
AMN