በደቡብ ኮሪያዋ ቹንቹን ከተማ በተካሄደ ዓለማቀፍ የታዳጊዎች የስነ ጥበብ የስእል ውድድር አዲስ አበባን ወክለው አሸናፊ ለሆኑት ታዳጊዎች እውቅና እና ሽልማት ተበረከተላቸው።
በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ ኤምባሲ ምክትል ተጠሪ የሆኑት ኪም ሂዮን ዱ በቹንቹን ከተማ ከንቲባ ስም ሽልማቱን ለአሸናፊ ታዳጊዎች አስረክበዋል፡፡
በኢትዮጵያ እና በደቡብ ኮሪያ መካከል ያለውን ታሪካዊ ወዳጅነት ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ መሆኑን በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ ኤምባሲ ምክትል ተጠሪ ኪም ሂዮን ዱ በሁለቱ እህት ከተሞች ማለትም አዲስ አበባ እና ቹንቹን ከተሞች መካከል ያለውን ሁለተናዊ ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።