አዲስ አበባ በራሱ ገቢ የሚተዳደር የራሱን ገቢ የሚወስን ትልቅ ከተማ ነው። ስለዚህ ገቢን በሚመለከት በራሱ ምክር ቤት የሚወያይበት ይሆናል ፤
– ፕሮፐርቲ ታክስ ኢትዮጵያ ውስጥ አልተጀመረም፤ አዲስ አበባም አልጀመረም ፤
– አዲስ አበባ የጀመረው የጣሪያ እና ግርግዳ የሚባል ከዚህ ቀደም የነበረው እና በየጊዜው እየተሻሻለ የመጣን ህግ ዘንድሮ ማሻሻያ አድርገዋል፤
– ይህ የተሻሻለው የጣሪያ እና የግድግዳ ግብር ማለት ፕሮፐርቲ ታክስ ማለት አይደለም፤ እሱን አዋጁን ስናይ በዝርዝር የምናይ ይሆናል ፤
– ይሄ የታክስ ምንጭ በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት አምጥቶ ያልተገባ ሀብት ወስዶ ከሆነ ቅሬታ የሚሰማበት ስርአት ስላለ በዚያው ስርአት ቅሬታ ቀርቦ ሊታይ ይችላል።