በከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የመሰረተ ድንጋይ የተቀመጠው በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የልቤ ፋና ትምህርት ቤት አካባቢ 35 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃና ለሚኖሩ አባወራዎች መኖርያ ቤት እንደ አዲስ በአራት ዘመናዊ ብሎኮች የመገንባት ስራ ለአንድ አመት ያክል በፍርድ ቤት እግድ ተጓቶ ቆይቶ ነበር።
ይህ ግንባታ በከፍተኛ ትንቅንቅ የፍርድ ቤት እግዱ ከተነሳ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የግንባታ ስራው በፍጥነት ተከናውኖ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሷል።
ሲጠናቀቅ 80 አባወራ እንዲይዝ ተደርጎ እየተሰራ ያለው ይህ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅና ለነዋሪዎች የሚተላለፍ ይሆናል፡፡
ጀምሮ መጨረስ ብቻ ሳይሆን በፍጥነትና በጥራት በመጨረስም አዲስ ባህልን ለትውልዱ እናስተላልፋለን!!