የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግል ማህበር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የሶስትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ በተካሄደው የሶስትዮሽ ስምምነት በዋናነት ሶስቱ አካላት ስፖርትን በመዝናኛና በቱሪዝም መዳረሻዎች ለማስፋፋት እና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ፣ ማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አጠናክሮ ለመቀጠል፣ የስፖርት ቱሪዝምን ለማሳደግ እና የከተማዋን ሁለንተናዊ የስፖርት እንቅስቃሴ ለማሳደግ በጋራ ለመስራት የተስማሙባቸው ተግባሮች ናቸው።
በሶስትዮሽ የስምምነት ሰነድ የፊርማ ስነስርዓቱ ላይ አቶ አብርሀም ታደስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ፣ ዶ/ር ሂሩት ካሳው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ እና ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ ተገኝተው ተፈራርመዋል።
በቅርቡም ሶስቱ አካላት በጥምረት በእንጦጦ ፓርክ የመጀመሪያውን የፖርክ ሩጫ በኢትዮጵያ በድምቀት እንደሚካሄድ በስምምነት ፕሮግራሙ ላይ ተገልጿል።