የከተማዋን ብልፅግና ለማረጋገጥ እየተጋ ያለው የከተማው አስተዳደር አዳዲስ የትራንስፖርት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የተለያዩ አማራጮችን ነድፎ ወደ ተግባር ገብቷል፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ የፈጣን ባስ ትራንስፖርት አገልግሎት ነው፡፡
BRT ሲስተሙ ደህንነቱ የተጠበቀ ፣ ምቹ እና አስተማማኝ የአውቶቡስ አገልግሎት በማቅረብ የከተሞችን የትራንስፖርት ስርዓት በማዘመኑ ይመሰገናል፡፡
በአጭር ጊዜ የሚተገበር እና እንደ ቀላል ባቡር አገልግሎት ካሉ የትራንስፖርት አማራጮች ጋር ሲነፃፀር ወጪ ቆጣቢ መሆኑ በአዲስ አበባ ለመተግበር ተመራጭ አድርጎታል፡፡
በአዲሱ የከተማዋ የትራንስፖርት ማስተር ፕላን 15 የፈጣን አውቶቡስ አገልግሎት ኮሪደሮች ሲኖሩ ከዊንጌት-ጀሞ የሚዛልቀው የB2 ፕሮጀክት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተጥሏል፡፡
የፈጣን አውቶቡስ አገልግሎት/BRT/ ሲስተም ከነባር መንገዶች የሚለየው:-
አውቶቡሶች ብቻ የሚጠቀሙበት የተለየ መንገድ መሆኑ፣ የራሱ የተለየ ጣቢያ ያለው መሆኑ፣ የጣቢያው መሬት ከአውቶቡሶች ወለል ጋር እኩል መሆኑ፣ በመጋጠሚያዎች ላይ ለአውቶቡሶች ቅድሚያ መስጠቱ፣
አውቶቡሶቹ በየደቂቃው ልዩነት በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ በየጣቢያው መድረሳቸው እና
የክፍያ ስርዓቱ ወደ ጣቢያው ከመገባቱ በፊት በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች የሚፈፀም መሆኑ ናቸው፡፡
አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስና ውብ ለማድረግ እንተጋለን !!!